ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከኤክስትራ ቴንደር (www.extratenders.com)፣አፍሮ ቴንደር (www.afrotender.com) እና ቱ መርካቶ ዶት ኮም (www.2Merkato.com) ድህረገፅ በመግባት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተሽከርካሪዎቹን ለማየት ተጫራቾች መታወቂያቸውን በመያዝ አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህስስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ማየት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በመዝጊያው ቀን ታህስስ 30 እስከ ጠዋት 6፡30 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለስ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአንድ ተሽከርካሪ የመግዣ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ይከፈታል፡፡
5. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡
ኢትዮ ቴሌኮም